የመረጃ እና ድጋፍ ማዕከል የበይነ መረብ የትምህርት ኮርሶችን ለማኘግት የተጠቃሚ መለያ ከእኛ ጋር ማስመዝገብ እና መለያዎን በመጠቀም ወደ ድረገጹ መግባት ያስፈልግዎታል።

 

Learning

 

የመረጃ እና ድጋፍ ማዕከሉ "ለጥቃት ጥበቃ ያሻል" በሚል ርዕስ ተከታታይነት ያላቸው አምስት የበይነ-መረብ የስልጠና ሞጁሎችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። ሞጁሎቹ "ፋሚሊ ሄልዝ ፍሮንቲየርስ" (ኤፍ.ኤች.ኤፍ) ተብሎ የሚጠራ ምናባዊ የሆነ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ሁኔታ ተኮር የትምህርት አሰጣጥ ይጠቀማሉ። ሠልጣኞቹ ድርጅታቸው ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆንና ከጥቃት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን መለየት እንዲችሉ እራሳቸውን እንደ FHF የቡድን አባላት በመቁጠር አምስቱን ሞጁሎች ይወስዳሉ።

እያንዳንዱ ሞጁል በጥቃት ጥበቃ ማሳሰቢያዎች የታጀበ ሲሆን የሞጁል ትምህርቱ ከተጠናቀቀ በኋላ እስከ ሁለት ወራት የሚዘለቅ ተጨማሪ የትምህርት ማሳሰቢያዎችን ያካታል።

እነዚህ ሞጁሎች በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች (CSOs) ውስጥ የሚሰሩ የጥቃት ጥበቃ ሙያተኞች ባልሆኑ ነገር ግን   ጥበቃን በተመለከተ ቁልፍ እውነታዎችን ለመማር፣ ዕውቀትን ለማግኘት፣ ስራዎችን ሰርተው የ RSH የምስክር ወረቀት ለማግኘት ተለዋዋጭ መንገዶች በሚያስፈልጓቸው ሰራተኞች ላይ ያተኮሩ ናቸው። የጥቃት ጥበቃ ልዩ ባለሙያዎችም ቢሆኑ ቴክኒካዊ መረጃዎችን፣ ጠቃሚ የሆኑ የመረጃዎች ምንጮችን እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሚገጥሟቸውን የጥቃት ጠበቃ ተግዳሮቶችን በተመለከተ ክህሎቶችን በማግኘት ይጠቀማሉ። በልማቱ እና በሰብአዊ ዘርፉ ላይ የሚሰሩ ሁሉ እነዚህ ሞጁሎች ጠቃሚ ሆነው ያገኟቸዋል። 

 

ማስጠንቀቂያ

እነዚህ ሞጁሎች ሊያስጨንቁዎ የሚችሉ ይዘቶችን ይዘዋል።

የመጀመሪያዎቹ አራት ሞጁሎች በፈረንሳይኛበአማርኛበስዋሂሊበሃውሳ እና በአረብኛ ተዘጋጅተው ይገኛሉ። ሞጁሎች 1-2 በፖርቹጊስ ተዘጋጅተው ይገኛሉ። የተቀሩት ትርጉሞች በ2022 ተዘጋጅተው ይቀርባሉ።

ለሞጁል 1 መግቢያ

የጥቃት ጥበቃ ጉዳዮች ሞጁል 1:- ከጥቃት ጥበቃ ያሻል ሞጁል 1 መጀመር or መግቢያ/መጀመሪያ

የጥቃት ጥበቃ ዙሪያ ከተዘጋጀው ባለአምስት ክፍል የበይነ-መረብ ተከታታይ ትምህርት ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ሞጁል ነው። ተከታታይ ትምህርቱ እውነተኛ የጥቃት ጥበቃ ጉዳዮችን በሚመለከተው ብሔራዊ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት በFHF ታሪክ አማካይነት ቁልፍ የጥቃት ጥበቃ ፅንሰ-ሀሳቦችን  . - ያስተዋውቃል።

የእርስዎ ድርሻ ከኤፍ.ኤች.ኤፍ ቡድን አባላት ጋር አብሮ በመስራት የወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃት እና ትንኮሳ አዘል ጥቃቶችን የመከላከል ስራ አዲስ በሚጀመር ፕሮግራም ውስጥ አንድ ዋና ጉዳይ ሆኖ እንዲካተት ማስቻል ነው።

ከትምህርቱ የሚጠበቁ ዉጤቶች

ይህ ሞጁል የሚከተሉትን ለማድረግ ይረዳዎታል፡-

  • ከጥቃት ጥበቃ/ከለላ ጋር የተያያዙ ቃላትን ለመተርጎም
  • በአንድ ድርጅት ውስጥ ከጥቃት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ሃላፊነቶችን ለመረዳት
  • የስራ ቦታ ባህሪያት ለጥቃት ጥበቃ ያላቸውን አስፈላጊነት ለመገንዘብ

ጥናቱ የሚወስደው ጊዜ:- 30 ደቂቃዎች

 

ለሞጁል 2 መግቢያ

የጥቃት ጥበቃ ጉዳዮች ሞጁል 2 /ከጥቃት ጥበቃ ያሻል ሞጁል 2 ከአጋሮች ጋር ስራ መጀመር

በሞዱል 2 ውስጥ ሰልጣኞች FHF ለአዲስ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄን በሚያቀርብበት ፣ ከጥቃት ጥበቃ የድርጅታዊ አቋም ዝርዝር ጥናት ግምገማ በሚያከናውንበት እና የፕሮግራም አጋሮችን በሚለይበት ወቅት አብረውት ይሰራሉ። በፕሮግራሙ አስተዳደር ዑደት ውስጥ  የጥቃት ጥበቃ ስለሚከናወንበት መንገድ እና ለጥቃት ጥበቃ ክንውን አደጋ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችም እንዲሁ ተዳሰዋል።

ከትምህርቱ የሚጠበቁ ዉጤቶች

ይህ ሞጁል የሚከተሉትን ለማድረግ ይረዳዎታል፡-

  • ከጥቃት ጥበቃ ጋር የተያያዘ የድርጅታዊ አቋም ዝርዝር ጥናት  ለተቋማት እና ለአጋር ድርጅቶች የሚኖረውን ፋይዳ ለመረዳት፣
  • ደህንነትን የሚያስጠብቅ ፕሮግራም ለመንደፍ/ለመቅረጽ የሚያስችሉበፕሮግራም ዑደት ዉስጥ መካተት የሚገባቸውን ቁልፍ የሆኑ የጥቃት ጥበቃ ተግባራትን ለመለየት እና 
  • ደህንነትን ወደሚያጎናጽፉ አሰራሮች ለመሸጋገር ጠንካራ  የአመራር  እና የተቋማዊ/ድርጅታዊ አሰራር ባህል አስፈላጊነትን ለመገንዘብ

ጥናቱ የሚወስደው ጊዜ:- 1 ሰዓት

ሞጁሎቹን ሲያጠናቅቁ ስለተማሩት ትምህርት ያለዎትን ሀሳብ፣ ጥያቄዎችዎን እና አስተያየቶችዎን በበይነ መረብ  ማህበረሰቦች የውይይት መድረክ ላይ ከአቻዎችዎ ጋር መጋራት ይችላሉ።

 

ለሞጁል 3 መግቢያ

ሞጁል 3 የጥቃት ጥበቃ ያሻል፦ በአስተማማኝ መርሃግብሮች መስራት


በሞጁል 3 ውስጥ ተማሪዎች አዲሱ የህጻናት ክትባት መርሃ ግብር አስፈጻሚ አጋር የሆነውን ድርጅት ሹር ሄልዝ አፍሪካ ከፋሚሊ ሄልዝ ፍሮንቲየርስን ጋር በመሆን ጉብኝታቸውን ይቀጥላሉ ። የፕሮጀክት ጉብኝቶች ሲያቅዱ ምን ምን አስፈላጊ እንደሆነ ፣ እንዲሁም ስጋቶች በአግባቡ ተለይተው ካልታወቁ እና ካልተፈቱ ምን እንደሚከሰት ይወቁ።

ከትምህርቱ የሚጠበቁ ዉጤቶች
ይህ ሞጁል የሚከተሉትን ለማድረግ ይረዳዎታል፡-
•    ለአስፈጻሚው አጋር የጥቃት ጥበቃ የመስክ ክትትል ጉዞን ማዘጋጀት እና ማካሄድ ፣
•    ለተመረጡ ሰዎች ዝግጅትን በማስተናገድ የአጋር ኤጀንሲን መደገፍ ፤ እና
•    ይፋ ለተደረገ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት እና ሪፖርት ለማድረግ።


ጥናቱ የሚወስደው ጊዜ: 1 ሰዓት


ሞጁሎቹን ሲያጠናቅቁ ስለተማሩት ትምህርት ያለዎትን ሀሳብ፣ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በበይነ መረብ ማህበረሰብ የውይይት መድረክ ላይ ለአቻዎችዎ ማጋራት ይችላሉ።

 

ለሞጁል 4 መግቢያ

ሞጁል 4 የጥቃት ጥበቃ ያሻል፦ ቅሬታዎችን ማስተካከል

የጥቃት ጥበቃ ዙሪያ ከተዘጋጀው ባለአምስት ክፍል የበይነ-መረብ (ኢ-ለርኒንግ) ተከታታይ ትምህርት ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ሞጁል ነው። ከጥቃት ጥበቃ ጋር በተገናኙ ተጨባጭ ጉዳዮች ላይ የሚሰራ ፋሚሊ ሄልዝ ፍሮንቲየርስ (ኤፍ. ኤች. ኤፍ) የተባለ ብሄራዊ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅትን ምናባዊ ታሪክ መሠረት በማድረግ ተከታታይ ትምህርቱ ከጥቃት ጥበቃ ጋር የተያያዙ ቁልፍ ፅንሰ-ሃሳቦችን ያስተዋውቃል።

የእርስዎ ሚና የኤፍ ኤች ኤፍ ቡድን ለጥቃት ጥበቃ ቅሬታዎች ምላሽ ሲሰጥ፣ ከመርማሪ ጋር ሲሰሩ እና የጥቃት ጥበቃ ልምዶቻቸውን ውስጣዊ ክለሳ ሲያደርጉ ከእነርሱ ጋር መሳተፍ ነው።

ከትምህርቱ የሚጠበቁ ዉጤቶች

በዚህ ሞጁል ውስጥ የጥቃት ጥበቃ ሂደቶችን በተመለከተ ከፋሚሊ ሄልዝ ፍሮንቲየር (ኤፍኤችኤፍ) ጋር ይቀጥላሉ። ሞጁሉ የጥቃት ጥበቃ በምን ሁኔታ ሽፋን እንዳገኘ ይመለከታል፡

  • የጥቃት ጥበቃ ክስተት ሪፖርት መቀበል እና የመጀመሪያ ግምገማ ማድረግ ፤
  • የምርመራውን ሂደት መደገፍ ፤ እና
  • ትምህርቶችን ለመማር እና ልምድን ለማሻሻል የውስጥ የጥቃት ጥበቃ ግምገማ ማዘጋጀት እና ማካሄድ።

የጥናት ጊዜ፦ 45-60 ደቂቃዎች

የመረጃ እና ድጋፍ ማዕከል የበይነ መረብ የትምህርት ኮርሶችን ለማኘግት የተጠቃሚ መለያ ከእኛ ጋር ማስመዝገብ እና መለያዎን በመጠቀም ወደ ድረገጹ መግባት ያስፈልግዎታል።

የመረጃ እና ድጋፍ ማዕከል ተጠቃሚ መለያ ከሌለዎት እዚህ ጠቅ ያድርጉ

ቀድሞውኑ የመረጃ እና ድጋፍ ማዕከል ተጠቃሚ መለያ ካለዎት እዚህ ጠቅ ያድርጉ