ወደ የኢትዮጵያው የደህንነት ጥበቃ መረጃና ድጋፍ ማዕከል የዜና መጽሔት እንኳን በደህና መጡ! ዋና ዋና ዜናዎቻችን፣ መረጃዎቻችንና አገልግሎቶቻችን እዚህ ይገኛሉ፡-

Button with text saying Top News.

 

  1. አዲሱ የኢትዮጵያ ማዕከል ድረ ገጽ ይፋ ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያው ማዕከል ድረ ገጽ ከቀድሞው በተሻለ መልኩ ለተጠቃሚዎች የሚመች እንዲሆን እና በብዙ የሀገርኛ ቋንቋዎች እንዲገኝ አድረገን እንደገና ቀርጸነዋል፡፡
  2. የሰብአዊ  ምላሽ ገጽ (ከማዕከሉ ድረ ገጽ ጋር) ተሳሰረ፡፡  የኢትዮጵያ የወሲባዊ ብዝበዛ እና ጥቃት መከላከል (PSEA) ኔትዎርክ ድረ-ገጽን በዚህ የኢትዮጵያው ማዕከል ገጽ ላይ በቀጥታ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡
  3. የኢንተር አክሽን ማኅበረሰብ-አቀፍ የደህንነት ጥበቃ ስእላዊ መሣሪያዎች ስብስብ (ቱልኪት) በእንግሊዝኛ፤ በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በሶማሊኛ እና በኦሮምኛ ይገኛል፡፡

 

Button with text saying Top Resources.

 

  1. የደህንነት ጥበቃ ጉዞ፡- የደህንነት ጥበቃ መግቢያ ፤ የደህንነት ጥበቃ ምን ማለት እንደሆነ እና ከወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃት እና ጾታዊ ትንኮሳ የደህንነት ጥበቃ ለማድረግ የሚያስችሉ ቁልፍ የሥራ ዘርፎችን እንዴት ማጠናከር እንደሚገባ አጠቃላይ ዕይታ እንዲኖረን የሚያግዝ ሰነድ ነው፡፡
  2. የዓለም-አቀፍ ደረጃዎች አጭር መግለጫ፤ በጣም ተገቢነት ያላቸው የአምስቱ ዓለም አቀፍ የደህንነት ጥበቃ፣ እና የወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃት እና ጾታዊ ትንኮሳ ደረጃዎች (ስታንዳርዶች) ክለሳ፡፡ ደረጃዎቹን (ስታንዳርዶቹን) በሁሉም ቋንቋዎች እዚህ ላይ ሊያገኙአቸው ይችላሉ፡፡
  3. የደህንነት ጥበቃ ስጋት ዳሰሳ ማከናወኛ መሣሪያ/መመሪያ ይህ መሣሪያ ድርጅቶች ሊከሰቱ የሚችሉ የወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃት እና ጾታዊ ትንኮሳ ስጋቶችን መለየትና የመፍትሄ ስልቶችን መቀየስ እንዲችሉ የሚረዳ ነው፡፡ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ ይገኛል፡፡
  4. የሰው ኃይል እና በድርጅት ደረጃ የሚደረግ የወሲባዊ ብዝበዛና ጥቃት መከላከል መመሪያ፤ ይህ መመሪያ ወሲባዊ ብዝበዛና ጥቃትን የመከላከሉ ተግባር በሰው ኃይል አስተዳደርና በሌሎች ድርጅታዊ የሥራ ሂደቶች ውስጥ በአግባቡ መከናወኑን ለማረጋገጥ የሚያግዝ ነው፡፡ በእንግሊዝኛ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን/ሰነዶችን በኛ የኢትየጵያ ማዕከል/ቤተ መጻሕፍት በአማርኛ፣ በትግርኛ፣ በሶማሊኛ እና በኦሮምኛ፣ ወይም በዓለም-አቀፉ ማዕከል/ቤተ መጻሕፍት ማግኝት ይችላሉ፡፡

 

Image saying Top Multimedia

 

 

Button saying Top Services

 

 

አብረውን ይቆዩ!

ከኢትዮጵያው ማዕከል ትኩስ ዜናዎችን በራስዎ ቋንቋ፣ በቀዳሚነት መስማት ይችሉ ዘንድ ዜና መጽሔታችንን ለማግኘት ይመዝገቡ፡፡

በተጨማሪም በፌስ ቡክ፣ ትዊተር እና ሊንክድኢን ገጾቻችን ሊከተሉን ይችላሉ፡፡

ዜና መጽሔታችንን ወደዱት? እባክዎ ን ይህንን ማስፈንጠሪያ  ለባልደረባዎችዎና ለሌሎች ያጋሩ!

 
 

Safeguarding Essentials